About

በዚህ ድህረገጽ ላይ የሰፈሩት ይዘቶች በሙሉ ቀደምት ቅዱሳን አባቶቻችን አዘጋጅተው ለእኛ ያስተላለፉልንን  ባለንበት ዘመን በቤተ ክርስቲያን  ውስጥ በቅዳሴ ጊዜ ፤ በክብረ በዓላት ሥራዓተ ማኅሌት ሂደት  ምእመናን በሚዘጋጀው በኢሌክትሮኒክ ማሳያ (Screen) እየተመለከቱ  ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ፤ እንዲሁም በመዝሙር ቅዱስ እግዚአብሔርን ፣ ቅድስት እመቢታችን ድንግል ማርያም ፣ ቅዱሳን መላእክት ሲመሰገኑና ፤ ጻድቃንና  ቅዱሳን ሰማዕታት ሲዘከሩ ሙሉ ተሳታፊ እንዲሆኑና ከበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው።

 እንዲሁም ስልክን ጨምሮ በማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ላይ የሚፈለጉትን በማውረድ ለተለያዩ አገልግሎትች    ማዋል ይቻላል። እኔ እንደማንኛውም ምእመን እንጂ ካህን አይደለሁም። ይህ ዝግጅቴ በአባቶች ካህናትና በወንድሞች ዲያቆናት ዓይን ሲታይ  ብዙ ስሕተቶች ሊኖርበት ይችላል። አስተያየቶቻችሁን ብትልኩልኝ ያለመታከት ዕርምት ላደርግ እችላለሁ።

ጌታሁን ተሾመ (ኃይለ ገብርኤል)